
የእስምና መስረቶች አምስት ናቸው። እነዙህም እንደሚከተለት ይሆናሉ። ሸሃዳ፡ ሰላት፡ ዘካት፡ ሃጅ እና ዖም ናቸው። ለዚህም ማስረጃው ፡ አብደላህ ኢብን ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዓ.) ነቢዩ (ስ.ዓ.ወ.) እንዲህ ሲሉ ስምቻለሁ ብለዋል፡ “ እስሌምና የተገነባው በአምስት ነገር ላይ ነው፡፡ ከአላህ ሌላ የሚመለክ አምላክ የለም ሙሃመድም (ስ.ዓ.ወ.) የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር ፣ስላትን መስገድ፣ ዘካትን መክፈል፣ ሃጅ ማድረግ እና የረመዳንን ወር መጾም ናቸው።” (ቡኻረና ሙሰሊም ዘግበውታል)
ከዚህ በመቀጠል እነዚህን አምስቱን የእስልምና መሰረቶች በዝርዝር እንመለከታለን።
Click here to read more in PDF format


ምስጋና ለአላህ ይገባው። ለአለማት ጊታ ። እሱን ለማምለክ ለበጎ ስራና አላማ ፈጥሮናል። ለዚህም ሲል አላህ ሱ.ወ በየግዚው መልክትኞችን ተውሂድ እንዲያስተምሩ ሰዎችን ወደ “እኸላስ” እንዲጠሩ በየዘመናቱ ልካል። ተውሂድ ማለት አላህን በብቸኝነት መገዛት ማለት ነው። (የማጋራት ተቃራኒ) ተውሂድ እጅግ ሰፊና ምሉዐ እና ውብ ማራኪ ነው። አላህ ሱ.ወ ተውሂድን እንደ ሰማይ መስሎታል፤ ተውሂድን የተወን ደሞ ከሰማይ ወደ መርት እየተምዘገዘገ በሚወድቅ ነገር መስሎታል። ምከንያቱም ከኢማን ምጥቀት ወደ ኩፍር ዝቅጠት እያሽኮለኮል ነውና። አብዛኞቱ የእውቀት ባለቤቶች ተውሂድን በሶስት ይከፍሉታል፤
-ተውሂድ አር-ሩቡቢያ ( የጌትነት አምልኮት)
-ተውሂድ አል-ኡሉሁያ ( አምልኮታዊ ኢባዳ)
-ተውሂድ አስማኡላሂ ወሲፋቲሂ (የአላህ ስሞች ባህሪያት አምልኮ)
Click here to read more in PDF format
